ጥቅምት 16 2010 ዓ/ም ድጋሚ የተደረገውን የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ኡሁሩ ኬንያታ ኬንያን ለሁለተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሓላ ፈጸሙ።
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቅምት 16 በድጋሚ የተደረገውን የኬንያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት አፀና። በዚህም ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ያሸነፉትን ምርጫ አፅድቋል።
ኬንያ፣ የሶማሊያ ስደተኞች ይኖሩበት የነበረውን የደዳብ ካምፕ ሠፈሮች እየዘጋች መሆኗን ስደተኞች ተናገሩ። ባለፈው ዓመት "ካምብዮስ" የተባለ የደዳብ ሰፈር የተዘጋ ሲሆን፥ በሚቀጥለው ዓመትም “F2” የተባለው ሰፈር ሊዘጋ እንደሆነ ስደተኞቹ ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።
137 ኢትዮጵያዊያንን በሕገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ እንዲገቡ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ዛሬ ኬንያ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የኬንያ ፖሊስ ባለፈዉ አርብ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸዉ 137 ህገ ወጥ የኢትዮጵያዉያ ፍልሰተኞች ላይ ትላንት ከሰዓት ብይን ሰጠ። በፍርዱም እያንዳንዳቸዉ 300 የአሜርካን ዶላር ወይም የ 6ወር እሥራት ተላልፎባቸዋል።
የኬንያ ምርጫ ቦርድ የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ያጣጣሉትን ምርጫ ውጤት ዛሬ ይፋ አደረገ። በምርጫው ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ ደምፅ አግኝተው ማሸነፋቸውን የኬንያ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽነር ዋፉላ ቸቡካቲ ገልፀዋል።
በናይሮቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሠብ ተወካይ የኢትዮጵያ መንግሥት የኬንያ ፖሊስን ተጠቅሞ በስደተኛው ላይ ጫና ማድረጉን አላቆመም በማለት ተናገሩ።
ካሎበዬይ በሰሜን ምዕራብ ኬንያ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ አዲስ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ነዉ።
የኬንያ ሲቪል ማኅበረሰብ ጥምረት የኬንያ የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ላይ ምርመራ እንዲካሄድ በመጠየቅ ትላንት ማምሻዉ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን የፊታችን ጥቅምት 7 አዲስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚያካሄድ ገልጿል፡፡
የአለፈዉ ዓርብ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት ውሳኔ በኬንያታ ደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታ ሲያሳድር በተቀናቃኛቸዉ በራይላ ደጋፊዎች ዘንድ ግን ልዩ ደስታን ፈጥሯል።
ኬንያ በቅርቡ ያካሄደችው ፕሬዘደንታዊ የምርጫ ሂደት ፍትሃዊ አልነበረም ሲል የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውጤቱን ውድቅ አድርጓል፤ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ወስኗል።
ኬንያ ፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም የሚከለክለዉን ህግ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች
14ኛዉ የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ዕድገት ጉባኤ በናይሮቢ በመካሄድ ላይ ነዉ።ትላንት በተጀመረው ጉባኤ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙንን ጨምሮ የበርካታ አገሮች መሪዎች ተገኝተዋል።
ናዝራዊ ኢያሱ አባቱ ኢትዮጵያዊ እናቱ ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው። ወላጆቹ እኤአ ከ2001 ዓ. ም. ጀመሮ በኬንያ በስደት ነው የኖሩት። ኬንያ እንደመጡ ከናይሮቢ 180 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘዉ ናሮክ ከተማ ኑሯቸውን መሰረቱ።
የኬንያ የሕግ ባለሞያዎች ማህበር ከተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጋር በመሆን በናይሮቢ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ። በተቃዉሞዉ ሰልፍ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የህግ ባለሞያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ግለሰቦች የተሳተፉበት ሲሆን መንግስት በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለዉን ግድያ ለማስቆም የበኩሉን መወጣት አልቻለም ሲሉ ተችተዋል።
የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኬንያ ጉብኝት ላይ ናቸዉ። ሮብ ማታ ናይሮቢ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኬንያዉ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር የጋራ ዉይይት ካደረጉ በኋላ በማዕድን (ተፈጥሮ ጋዝ)፣ በጤና ፣ በስፖርት፣ በድምበር ጥበቃና በትምህርት ዘርፍ 5 ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። ሁለቱ መሪዎች ከኬንያ የድንበር ግዛት ለሙ እስከ አዲስ አበባ ሊዘረጋ የታሰበዉን የነዳጅ ቱቦ መስመር ስምምነቱን በዚህ ዓመት መጨረሻ ለመፈራረም ከመግባባት ደርሰዋል።
የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ መዘጋት ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እንደሚጥለው ቁጥራቸዉ አነስተኛ የሆነ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የኤርትራ፣ የቡሩንዲ እንዲሁም የሌሎች ሃገሮች ስደተኞች ገለጹ።
ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ታንዛኒያ በሕገወጥ መንገድ የገቡት 71 የኢትዮጵያ ዜጎች በዳሬሰላም ፍርድ ቤት ቀርበዉ ለሁለት ሳምንት ቀጠሮ ተሰጣቸዉ።
ተጨማሪ ይጫኑ