በሶማሌ ክልል ጂጂጋ ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከገቡ በኋላ የነበሩት ጥቃቶች ቆመው አንፃራዊ መረጋጋት ቢኖርም ከፍተኛ የሆነ የምግብና የመጠጥ ችግር መከሰቱን ነዋሪዎች ገለፁ።
ከቅዳሜ ጀምሮ በውጥረት ውስጥ ወደ ሰነበተችው ሶማሌ ክልል ጂጂጋ ከተማ ማምሻውን የመከላከያ ሠራዊት በመግባቱ ከተማው እየተረጋጋ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በአማራ ክልል በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ ቅላዥ ከተማ፤ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ያነሱ ነዋሪዎች በአደራ ፖሊስ ጣቢያ ያስቀመጧቸው የዞን አመራሮችና የፀጥታ ኃላፊዎች በመለቀቃቸው ግጭት ተፈጠሮ አራት ሰዎች ቆሰሉ። ነዋሪዎችና የዞን አመራር ያነጋገረችው ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።
በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችንና ሞቶችን ለማስቀረት ሀገሪቱን በፍጥነት ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማስገባትና ፍትሐዊና ሕጋዊ ተቋማትን መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ያነጋገርናቸው ባለሞያዎች ገለፁ።
ከእስር የተለቀቁት ሰዎች መልሰው እንቋቋሙ ምን ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል? ድጋፉንስ ሊሰጣቸው የሚገባው ማነው? በሚሉና በሌሎች ከእስር የተለቀቁ ሰዎችን በሚመለከቱ ጉዳዮች የተደረገ ውይይት።
ለሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ና የልዑካን ቡድናቸው ይዘው አዳራቸውን ሐዋሳ ከተማ ያደርጋሉ። በአሁኑ ሰዓትም የእራት ግብዣ እየተደረጋላቸው ሲሆን ነገ ጠዋት በኦሮሞ ባሕል የተዘጋጀ የቁርስ ሥነ - ስርዓት ይጠብቃቸዋል ተብሏል።
ልጆቻቸው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው እንደሚገኙ የገለፁ የእስረኛ ቤተሰቦች ዛሬም ወደ ውስጥ ገብተው ስንቅ ማቀበል እንዳልቻሉ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
መቀመጫውን ኤርትራ ያደረገውና በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ አንጃ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲያደርግ የነበረውን የትጥቅ ትግል በጊዜያዊነት ማቆሙን ዛሬ አስታወቀ። በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ሰሞኑን በተፈፀመው ግድያና ሁከት ውስጥ እጁ እንደሌለበት ተናግሯል።
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐሙድ ኡመር የኢትዮጵያ ደኅንነት ኃላፊዎች በክልሎች አሠራሮች ላይ ነበሯቸው ያሏቸውን ጣልቃ ገብነት አብራሩ።ሸሽተን በአዲስ አበባ ተጠልለናል” ያሉ ወጣቶች በበኩላቸው፤ ፕሬዝዳንቱ ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማሸሽ የፈጠሩት እንደሆነ ገልፀው “በክልሉ ለተፈፀሙትና እየተፈፀሙ ላሉት ዘግናኝ ግፍና በደሎች እርሳቸውም ተጠያቂ ናቸው”ብለዋል።
ኢትዮጵያና ኤርትራ በመካከላቸው የነበረው የውጥረት ጦርነት በይፋ ለማስቆም ስምምነት መፈረሙን አስታወቁ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ልዩ ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ስምምነቱን ያብራሩልናል። በተያያዘም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ከጨበጡ አንድ መቶ ቀናት ሊደፍኑ ጥቂት ቀናት የቀራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬም በአርባ ምንጭ የድጋፍ ሰልፍ ተደርጎላቸዋል።
በሶማሌ ክልል “ኦጋዴን” በተባለው እስር ቤት ሰዎች በዘፈቀደ እየታሰሩ እጅግ አሰቃቂ ተግባር ይፈፀመብቻዋል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ወች ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።በዚህ በማይቋረጥ የመብት ጥሰት ውስጥ የመንግሥት ባላሥልጣናት እጃቸው አለበት ብሏል። የሶማሌ ክልል መንግሥት ሪፖርቱ ከእውነት የራቀ ነው ሲል ማስተባበያ ሰጥቷል።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፤ በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ባሰባሰበው ሪፖርት ዘግናኝ የሆኑ ምርመራዎች የሚፈፀሙባቸው እርስ ቤቶች፤ የተዘጋውን ማዕከላዊ ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል፣ በአማራ ክልል፣ በሶማሌ፣ በደቡብ እና በሌሎች ባልታወቁ እስር ቤቶች ጭምር እንደሚፈፀሙ አስታውቋል።
በመተማ የእርሻ ቦታ በሱዳን ታጣቂዎች የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አስክሬን ዛሬ ወደ ቤተሰቦቻቸው መምጣቱን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለፁ።
ዮናስ ጋሻው ደመቀ ባለፈው ሣምንት ከእስር የተፈታ ወጣት “በተፈፀመብኝ ለመናገርና ለመስማት የሚከብድ ኢሰብዓዊ ሥቃይ ዛሬ ከዊልቸርና ክራችስ (ከወንበርና ከምርኩዞች) ውጪ ራሴን ችዬ መንቀስቅቀስ የማልችል ሰው ሆኛለሁ” ይላል። (ጽዮን ግርማ በተከታዩ ዘገባ ታሪኩን ይዛለች።)
በመተማ "ደለሎ ቁጥር አራት”በተባለ የእርሻ ቦታ ላይ በእርሻ ሥራ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በሱዳን ታጣቂዎች መገደላቸውን፣ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ጨምሮ ደግሞ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎችና የሆስፒታል ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ዐሥራ ሦስት ዓመታትን በእስር ያሳለፈው መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬ ካለፈባቸው ከባድ ጊዜያት መካከል የእናቱን ማረፍ የሰማበት ዕለት እንደሆነ ይናገራል።ጽዮን ግርማ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
የአሶሳ ከተማ ከንቲባ በዛሬው ዕለት የቆሰሉ ሰዎች አሶሳ ከተማ ሆስፒታል መግባታቸውን ተናግረዋል።
በቤንሻንጉል ክልል ግጭት አስር ሰዎች መሞታቸው ከ40 በላይ መቁሰላቸው ታውቋል።
በግጭቱ የሰው ሕይወት መጥፋቱና መቁሰሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ማኦ ኮሞ ወረዳ ቶንጎ ከተማ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ የወጡ ነዋሪዎች በክልሉ ልዩ ፖሊስ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት የሁለት ሰው ሕይወት ማለፉንና 40 ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎችና የአጎራባች ወራዳ ፖሊስ ኃላፊዎች ገለጹ።
ተጨማሪ ይጫኑ