ይህ የዛሬ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መመሥረቻ ቻርተርና ሰባ ዓመት በሀገሮች መካከል ከተፈረመው የሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ድንጋጌ ጋር የተያያዘ ዕለት ዘንድሮ በዓለም ደረጃ ሲታሰብ ሃያኛ ዓመቱ ነው። ጽዮን ግርማ በኢትዮጵያ በየእሥር ቤቱ ይደርስባቸው የነበሩ የከፉና የሥቃይ አያያዞችን ያካፈሉን ሰሞኑን የተለቀቁ የቀድሞ እሥረኞች ታሪክ ይዛ ተከታዩን ዘገባ አሰናድታለች።
በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ለመግለጽ የሚከብድ ግፍ ተፈጽሞብኛል ያለውን በቅርቡ የተፈታውን የአየር ኃይል አብራሪ የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን አነጋግረነዋል።
በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ላይ የሚካሄደው ምርመራ መጀመሩን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ጽዮን ግርማ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማልና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋን አነጋግራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ያዳምጡ።
የደረሰውን አደጋ በተመለከተ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማንንና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ስለ ፍንዳታው ማብራሪያ ሰጥተውናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ የጀመሩትን ለውጥ ለማበረታት በተጠራው በዛሬ ሰልፍ ላይ በእጅ ቦንብ 98 ሰዎች መቁሰላቸውን እስካሁን ግን ሕይወቱ ያለፈ ሰው ሪፖርት አለመደረጉን ፌደራል ፖሊስ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማልን አነጋግረናቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ የጀመሩትን ለውጥ ለማበረታት በመስቀል አደባባይ በተካሄደው በዛሬው ሰልፍ ላይ በእጅ ቦንብ 98 ሰዎች መቁሰላቸውን፣ እስካሁን ግን ሕይወቱ ያለፈ ሰው ሪፖርት አለመደረጉን ፌደራል ፖሊስ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማልን አነጋግረናቸዋል።
የተጀመረውን ለውጥ ለመደገፍ ዴሞክራሲን ለማበረታት በሚል በነገው ዕለት የተጠራው ሰልፍ በሰላም እንዲጠናነቅ “ይድረስ ለአዲስ አበቤዎች” የሚሉ መልዕክቶች እየተጻፉ ነው። መልዕክቶቹ ከግጭት እራቁ በሰላም ወጥታችሁ በሰላም ግቡ የሚል ይዘትም ያላቸው ናቸው።
ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ ታስረው የተፈቱ አባላት በበዙበት ኮሚቴ እየተዘጋጀ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማው ሰልፍ ፍቃድ ማግኘቱን አዘጋጆቹ ተናገሩ።
ባለፈው ሳምንት ግጭት በተቀሰቀሰባቸውና በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት በደረሰባቸው ሦስት የደቡብ ክልል ከተሞች የሚገኙ የወረዳና የዞን አመራሮች ኃላፊነት ወስደው ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ሊለቁ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተናገሩ።
አሸናፊ አካሉ በምዕራብ ጎጃም ሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ ውስጥ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት የግዢ ኃላፊ በነበረበት ወቅት በሽብር ወንጀል ተከሶ መታሰሩን ይናገራል። በእስር ላይ በነበረበት ወቅትም አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈፀመበት ይናገልፃል።
"የሦስተኛ ዓመት ትምሕርቴን ጨርሼ ወለጋ ቤተሰቦቼንለመጠየቅ መንገድ ጀመርኩ። መስከረም 3/1999ዓ.ም ካደርኩበት አዲስ አበባ ካራ ቆሬ የምትገኝው እህቴ ቤት ወጥቼ ከጓደኞቼ ጋራ ወደ አውቶብስ ተራ መንገድ ጀመርን። አንድ ፌርማታ እንደሄድን ተኩስ ተከፈተብን። ሦስቱ ወዲያው ሞቱ። እኔ አንድ እግሬ ተጎዳ። ፖሊስ ሆስፒታል ገባሁና ጤነኛው እግሬ ተቆረጠ። ሁለቱም ተቆርጦ ከእነ ቁስሎቼ ወደ ማዕከላዊ ተወሰድኩ"- አርብ ዕለት ከእስር የተፈታው ከፍያለው ተፈራ የተናገረው ነው።
ግጭትና መፈናቀልን ለመቅረፍ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ቀዳሚ መፍትሔው እንደሆነ ምሑራን ገልፁ።
በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የምሕንድስና ትምሕርት ክፍል ተማሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ጋራ በተያያዘ ተማሪዎች ባደረጉት ተቃውሞ በዩኒቨርስቲው ተጀምሮ የነበረው ፈተና መቋረጡን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ገለጹ።
በሀዋሳ፣ በወላይታና በወልቂጤ በተፈጠሩ ግጭቶች በሰዎችና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ታወቀ። አካባቢዎቹም ውጥረት እንደነገሰባቸው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። ለግጭቶቹ መባባስ ደግሞ የተጋነኑ መረጃዎች አስተዋጾ አላቸው ብለዋል። ከዚህ በላይ ሁኔታዎቹ እንዳይባባሱ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበትም አሳስበዋል።
በሀዋሳ ከተማ የተከበረውን የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የፊቼ ጨምበላላ ባህል ዋዜማ ተከትሎ የተፈጠረው ግጭት በዛሬው ዕለት ተባብሶ መዋሉን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለጹ። ግጭቱ ወደ ብሔር እንዲያድግ የሚፈልጉ አካላት እንዳሉ የሚናገሩም አሉ።
በትናንትናው ዕለት በሐዋሳ ከተማ የፊቼ ጨምበላላ በዓል ዋዜማ ላይ በተፈጠረ ግጭት፤ የሰው ሕይወት መጥፋቱን ከ30 የበለጡ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን በሐዋሳ ከተማ ያነጋግረናቸው ነዋሪዎች ገለፁ።
የምሕረት አሰጣጥና አፈፃፀም ሥነስርዓት ረቂቅ ዐዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል። ይህ ረቂቅ ዐዋጅ ምን ያካትታል? ጽዮን ግርማ በምክር ቤቱ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ዴታ አቶ አማኑኤል አብርሃም ጠይቃቸዋለች።
ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ምላሽ እንዲሰጣቸው አስፈላጊው ጥበቃም እንዲደረግላቸው አሳስቧል።
ከቀድሞው የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ብሪጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ጋራ የተደረገ ቃለ ምልልስ።
ከኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉት ነዋሪዎች የመፈናቀላቸው ምክኒያት “ፍርሃት እንጂ የፀጥታ ችግር አይደለም” ሲሉ የዞኑ የሰዲ ጨንቃ ወረዳ አስተዳዳሪ ገለፁ።ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ “የተደራጁ ኃይሎች ንብረት አቃጥለው፣ መሰረታዊ አገልግሎት እንዳናገኝ ከልክለው፣ ወደ ሀገራችሁ ሂዱ ብለው ሲያባርሩን ነው የኖርንበትንና ንብረት ያፈራንበትን መንደር ጥለን የተሰደድነው።” ይላሉ።
ተጨማሪ ይጫኑ