ከኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ከስምንት ወራት በፊት እንደተፈናቀሉ የሚናገሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከሁለቱም ክልሎች መፍትሔ ማጣታቸውን ተናገሩ።
"ለውጡ እንዳይቀለበስ በጥንቃቄ ሊያዝ ይገባዋል"- አቶ ዮናታን ተስፋዬ "እስረኖች በሙሉ ሊፈቱ ይገባል"- ጦማሪ ጌታቸው ሽፈራው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከእስር እንዲለቀቁ መወሰናቸውና ከዚያም በቤተመንግሥት ለውይይት መጋበዛቸው በመብት አራማጅ ወጣቶች ዘንድ እንዴት ይታያል? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ሦስት ወጣቶችን ያነጋገረቸው ጽዮን ግርማ ተከታዩን አጠናቅራለች።
በሲዳማ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት የተረፉ ሰዎች ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስባቸው አስፈላጊው እርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል ሲሉ በውጭ የሚገኘው የሲዳማ ተወላጆች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
በሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ሐሊላ መሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ በሚገኙ ሦስት መንደሮች በዝናብ ምክኒያት በደረሰ የመሬት መንሸራተት የ23 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሟች ቤተሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የኦነግ ወይም የግንቦት ሰባት አባል ናቸው በሚል የሽብር ክስ ቀርቦባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ተከሳሾች ከሌሎቹ ተነጥለው ከእስር አለመፈታታቸው እንዳስከፋቸው ከእስረኛ ቤተሰቦች የተወሰኑት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በሽብር ወንጀል ተከሶ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምሕር ጌታ አስራደ ከእስር እንዲፈታ ቤተሰቦቹ ተማፀኑ።
ወደ ስድስት የሚጠጉ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን የተቀበለውና ለዘጠኝ ጊዜ ታስሮ የተፈታው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ስቱዲዮአችን ተገኘቶ ከጽዮን ግርማ ጋራ ሰፋ ያለ አካሂዷል።በውይይቱ ስለቤተሰቡ፣ የእስር ሁኔታው፣ ስለጋዜጠኝነት ሞያው፣ ስለዴሞክራሲ ግንባታና ቀጣይ እቅዱ ተወያይቷል። ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ቪዲዮ ይመልከቱ።
ከእስር ከተለቀቁት መካከል ዶ/ር ፍቅሩ ማሩንና አቶ አግባው ሰጠኝን አነጋግረናቸዋል። አቶ አግባው ሰጠኝ ዛሬም ድረስ ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸው የሚገኙት ጓደኞቹ በሙሉ እስካልተፈቱ ደስተኛ እንዳልሆነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግሯል። በምርመራ ወቅት በምስማር ከመቸንከር ጀመሮ አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተናሯል።
በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ባጠናቀቅነው ሐሙስ ግንቦት 2 ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ስቱዲዮአችን ተገኝተው ከዝግጅት ክፍላችን ጋራ ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል።(ሙሉውን ቃለ ምልልስ ይመልከቱ)
በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ስቱዲዮአችን ተገኝተው ቃለ ምልልስ አካሂደዋል። በሕክምና ሥራ ከዚያም በመምህርነት አገልግለዋል። ከማኅበረሰብ ግልጋሎት እስከ ፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸውን ጉዞ ከጽዮን ግርማ ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ አብራርተዋል። ስለወጣትነት ዘመናቸውና ስለቤተሰባቸው የተወያዩትን በመጀመሪያው ክፍል ቀርቧል። በሁለተኛው ክፍል ቀሪውና ሙሉው ተካቷል።
በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ስቱዲዮአችን ተገኝተው ቃለ ምልልስ አካሂደዋል። በሕክምና ሥራ ከዚያም በመምህርነት አገልግለዋል። ከማኅበረሰብ ግልጋሎት እስከ ፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸውን ጉዞ ከጽዮን ግርማ ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ አብራርተዋል። ለዛሬው ስለወጣትነት ዘመናቸውና ስለቤተሰባቸው የተወያዩትን የመጀመሪያ ክፍል ይዘናል።
የተፈናቃዮቹ ጥያቄያቸው በተወለዱበት ክልል መልሶ መቋቋም መሆኑን በመጥቀስ ሌሎች ክልሎች በጎሳ ግጭት ለተፈናቀሉ ነዋሪዎቻቸው የሚሰጡትን እርዳታ አማራ ክልልም ሊሰጣቸው እንደሚገባ ይናገራሉ።
ፍርድ ቤቱ ዐሥራ አንዱን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ይሰናበቱ ብሏል። አራቱ በነፍስ መግደል ወንጀል ይከላከሉ ተብሏል። 23 ደግሞ ከነፍስ መግደል ወንጀል በመልሰ ባለው ወንጀል ይከላከሉ ተብሏል። ከጠበቆቹ አንዱ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ስለ ዛሬው የችሎት ማብራሪያ ሰጥተውናል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሱዳን ጉብኝታቸው ከፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋራ ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ያደረጉትን ውይይት በተመለከተ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለምን አነጋግረናል።
ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ዝም ለማሰኘት የምትጠቀምበትን አፋኝ ሕጎቿን ካላሻሻለች፣ የመጻፍና የመናገር ነፃነትን የምታፍንበትን የእጅ አዙር አስጨናቂ አካሄድ ካላስተካከለች፣ጋዜጠኞችን ከእስር መልቀቋ ብቻ ነፃ ሀገር ሊያሰኛት አይችልም ሲል ዋና ቢሮውን በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ በእንግሊዘኛው ምሕፃረ ቃል (CPJ) አስታወቀ።
በባሕርዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ተጠልለው የሚገኙት ከቤንሻንጉል ክልል ለተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች በቤተክርስቲያኑ እያገኙት ያሉት መፍትሔ ጊዜያዊ በመሆኑ ዘላቂውን መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉት ከመንግሥት ነው ሲሉ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ ገለጹ።
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ካማሽ ዞን፣ በለው ጃፎይ ወረዳ በግጭት ምክኒያት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ 527 አባወራዎች ባሕርዳር ከተማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በልመና ላይ እንደሚገኙ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
ጣና ሐይቅንና የአካባቢውን የተፈጥሮ ምኅዳር እየጎዳ የሚገኘውን እንቦጭ አረም ለማጥፋት በውጭ ከሚገኙ ኢትዮጵዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ግዩራን ጋራ በትብብር እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታውቋል።
በእስር ላይ የሚገኙት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የስዊድን ዜግነት ያላቸው የልብ ሃኪሙና የ“አዲስ የልብ ሕክምና ማዕከል” ባለቤት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ “አሁንስ ፍትህ አገኝ ይሆን?” ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ደብዳቤ ፃፉ።
በእስር ላይ እያሉ በቂሊንጦ ቃጠሎ በ"ሽብር" የተከሰሱት 38 ተከሳሾች "ይከላከሉ ወይንም በነፃ ይሰናበቱ" የሚለውን ብይን ለማዳመጥ ለትላንት ተይዞላቸው የነበረው ቀጠሮ በሌሉበት እንደተራዘመ ከጠበቆቹ አንዱ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ተጨማሪ ይጫኑ