በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

ፎቶ ፋይል - ተፈናቃዮች ዶሎ፣ ሶማሊያ ዳርቻ ወደሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ሲደርሱ እአአ 09/21/2022
ፎቶ ፋይል - ተፈናቃዮች ዶሎ፣ ሶማሊያ ዳርቻ ወደሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ሲደርሱ እአአ 09/21/2022

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት፣ በ58 ሀገራት የሚገኙና ከሩብ ቢሊዮን በላይ የሚኾኑ ሰዎች፥ በግጭት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአስከተለው መዘዝ፣ እንዲሁም በዩክሬን እየተካሔደ ባለው ጦርነት ሳቢያ፣ የከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ገጥሟቸው እንደነበር፣ አንድ ዐዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በአውሮፓ ኅብረት ትብብር በሚደገፈው፣ ዓለም አቀፍ የምግብ ቀውስ ሪፖርት የተሰኘው የረድኤት ድርጅቶች ኅብረት ይፋ በኾነው ጥናት፣ የምግብ ዕጦቱ በሰባት አገሮች ሞት ማስከተሉ ተገልጿል፡፡ እነኚኽ ሰባት ሀገራት፥ ሶማሊያ፣ አፍጋኒስታን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሄይቲ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ ሱዳንና የመን እንደኾኑ ጥናቱ አስፍሯል፡፡

የምግብ ዋስትና ዕጦት የገጠማቸውና አስቸኳይ ርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር፣ 258 ሚሊዮን መድረሱን ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡

በቦረና እና ጉጂ በድርቅ የተነሣ ሰው እንደ በሬ ተጠምዶ እያረሰ መኾኑን አርሶ አደሮች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00

ከአምስት ተከታታይ የዝናም ወቅቶች መታጎል በኋላ፣ በደቡብ ኦሮሚያ ዝናም ቢዘንምም፣ አሁንም አርሶ አደሮቹ፥ በዘር፣ በማዳበርያ እና በማረሻ በሬ ማጣት ችግር ላይ እንደ ኾኑ ተናግረዋል።

ዘር እና ማዳበሪያ፣ የምናርስበት በሬ የለንም፤ በፈንታው፣ ሰውን እንደ በሬ ጠምደን እያረስን ነው፤" የቦረና እና ጉጂ አርሶ አደሮች

በቦረና ዞን አንድ የድሬ ወረዳ አርሶ አደር፣ ያለፈው ድርቅ በርካታ የቁም ከብቶችን ስለ ፈጀ፣ አሁን ነዋሪው የሚያርስበት ከብት አጥቶ፣ ሰውን ልክ እንደ በሬ በመጥመድ የተገኘውን የእህል ዘር ለመዝራት እየሞከሩ መኾናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በጉጂም በተመሳሳይ፣ የዘር እና የማዳበሪያ አለመኖር ብቻ ሳይኾን፣ በአካባቢው ያለው የጸጥታ ዕጦት፣ የአርሶ አደሮቹን ችግር ማባባሱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ፣ አርሶ አደሮቹ፣ የእርሻ ግብአቶቹን እንዲያገኙ እየሠራኹ ነው፤ ይላል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG