በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

ፎቶ ፋይል፦ የተፈናቀያዮች መጠላያ ካምፕ፤ ዶሎ፣ ሶማሊያ ዳርቻ 09/19/2022
ፎቶ ፋይል፦ የተፈናቀያዮች መጠላያ ካምፕ፤ ዶሎ፣ ሶማሊያ ዳርቻ 09/19/2022

ሶማሊያ በበርካታ አሰርት ዓመታት ባልታየ ድርቅ በተጎዳችበት በአሁኑ ወቅት የሚሰጣት ሰብዓዊ ዕርዳታ ሊቀነስባት እንደሚችል የጠቆሙ የሃገሪቱ የዕርዳታ ሠራተኞች ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው አስታወቁ።

የለጋሾች መሰላቸት እና በዓለም ዙሪያ ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ቀውሶች ስላሉ ሶማሊያ የምታገኘው ሰብዓዊ ድጋፍ መጠን ሊቀንስባት እንደሚችል የረድኤት ሰራተኞቹ ሰግተዋል።

በቅርቡ የሶማሊያ መንግሥት እና የሰብዓዊ ረድዔት ድርጅቶች በዚህ እአአ 2023 በሶማሊያ 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎችን ለመርዳት የሚውል 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መማጸናቸው ይታወሳል።

በመጪው የመጸው ወቅት በቂ ዝናብ ካልጣለ እና የሰብዓዊ ረድዔት ድጋፉ ካልቀጠለ ከባድ ቸነፈር ሊከሰት ይችላል የሚል ሥጋት አሰምተዋል።

በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች የረሃብ ስጋት አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:08 0:00

በኢትዮጵያ ስድስት ተከታታይ ወቅት ዝናብ ላይጥል እንደሚችል በመገመቱ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለረሃብ አደጋ ሊጋለጥ ይችላል ሲል አክሽን አጌንስት ሀንገር የተሰኘው በአፍሪካ ቀንድ ረሃብን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ርዳታ ሰጪ ተቋም አስጠነቀቀ።

በኢትዮጵያ እስካሁን ቢያንስ 12 ሚሊየን ሰዎች ለሞት ለሚዳርግ የድርቅ አደጋ መጋለጣቸውን እና ከ4.5 ሚሊየን በላይ የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን የተቋሙ የኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቤዛ አበበ ተናግረዋል።

ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተጋለጡ ህፃናት ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨምረ መሄዱን ዳይሬክተሯ ጨምረው ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ በቀጠናው እየከፋ የሄደውን ድርቅ ለመቅረፍ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲወያይም ጠይቀዋል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG