በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

ድርቅ ሸሽተው በኬንያ የተጠለሉ የሶማሊያ ስደተኞች ለምግብ እጥረትና ኮሌራ በሽታ ተጋልጠዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:18 0:00

በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን አስከፊ ድርቅ ሸሽተው ከሶማሊያ ወደ ኬንያ ተሰደው በአሁኑ ወቅት መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙት ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እና የኮሌራ በሽታ መጋለጣቸው ተዘገበ።

የእርዳታ ተቋማት ለተረጂዎቹ የሚያውሉትን በቂ ገንዘብ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን እነኚህን ስደተኞች ለመርዳት መቸገራቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መፈናቀልና ጠኔ እየከፋ በመሆኑ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው የሱዳን ሕዝብ በያዝነው ዓመት ሰብዓዊ ዕርዳታ ይሻል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቀ፡፡

በምግብ ዕጥረት የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ለተከታታይ ሦስተኛ ዓመት ጨምሮ ታይቷል ሲል በተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ትናንት ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል፡፡

ከአምስት ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ አራት ሚሊዮን ሕጻናት እንዲሁም ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች ለጉዳት ከተጋለጡት ግንባር ቀደሙ ናቸው ያለው የኦቻ ሪፖርት፣ ሕይወት አድን ተመጣጣኝ ምግብ በዚህ ዓመት ያስፈልጋቸዋል ሲል አሳስቧል፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት የተፈጸመውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ በመቋረጡ ቀድሞውንም በረድኤት ድርጅቶች እገዛ ስታዘግም የነበረችው ሱዳን ችግር ውስጥ ወድቃለች፡፡

15.8 ሚሊዮን የሚሆነው ወይም ከሶስት እጅ አንዱ የሚሆነው የሱዳን ሕዝብ በዚህ ዓመት ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚሻና ቁጥሩም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ1.5 ሚሊዮን መጨመሩን ቢሮው አስታውቋል፡፡

በሃገሪቱ ያለው የሕክምናና የውሃ አቅርቦት አሳሳቢ ነው መባሉንም የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG