በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

“የከብቶቻችን ዋጋ ወደቀ” የቦረና አርብቶ አደሮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:56 0:00

ከብቶቻቸውን የሚገዛቸው በማጣታቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን የቦረና አርብቶ አደሮች ገለፁ። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የያቤሎ አካባቢ አርብቶ አደሮች፤ ድርቅ ካስከተለው ጉዳት የተረፉላቸውን ከብቶች እጅግ አነስተኛ በሆነ ዋጋ ለመሸጥ መገደዳቸውን አመለከቱ።

የቦረና ዞን የመስኖ ልማት እና አርብቶ አደር ጽህፈት ቤት በበኩሉ አሁን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ድጋፍ ለዚህ ምላሽ የሚሆን መፍትሄ መያዙን ገልጿል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ድርቅ የጎዳው ሶማሌ ክልል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:47 0:00

በሶማሌ ክልል በቀጠለው ድርቅ ምክኒያት የእንስሳት ሞት መጨመሩን ክልሉ አስታወቀ። አንዳንድ አካባቢዎች የበልግ ዝናብ ቢያገኙም ለአራተኛ ዓመት የቀጠለው የድርቅ ሁኔታ ባለመቀረፉ በተለይም በሦስት ዞኖች እንስሳት እየሞቱ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል።

ድርቁ ከበረታባቸው ዞኖች አንዱ በሆነው ዳዋ ዞን ብቻ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውና ከ300ሺ በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸውን ክልሉ አስታውቋል።

የዳዋ ዞን ነዋሪዎች ከችግሩ ስፋት አንጻር በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ጠቁመዋል። የሚችሉትን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የገለጸው የሶማሌ ክልል አቅም ያላቸው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG