በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

ደቡብ ክልል ውስጥ ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰው እርዳታ ይጠብቃል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ድርቅ አብዛኛው የወረዳው ነዋሪዎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውንና ከብቶቻቸውም እየሞቱባቸው መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ከድርቁ በተጨማሪ በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም አለመኖሩ ጉዳት እንዳባባሰውና በቂ እርዳታም እንዳልደረሳቸው አመልክተዋል።

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ140 ሺህ በላይ ሰው በአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የወረዳው አስተዳዳሪ አስታውቀዋል።

ደርቁን አስመልክቶ ከደቡብ ክልል ምክር ቤት ጋር መወያየታቸውን ለክልሉ መንግሥት ቴሌቪዥን የገለፁት የክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ጋንታ ጋምአ በክልሉ ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰው የምግብ እጥረት እንዳጋጠመው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

በድርቅ ምክኒያት በቦረና ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ እንስሳት እየሞቱ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

የደቡብ ኢትዮጵያው ቦረና ድርቅ ቦረና ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳትን ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል።

ከአስር ዓመት በፊት በአምስት አካፋዮች ተለይቶ የተመሰረተው ይህ ፓርክ የሜዳ አህያን ጨምሮ ቁጥራቸው የበዛ የተለያዩ ብርቅዬ እንስሳት ይገኙበታል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG