በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

“በጉጂ የተከሰተዉ ድርቅ አሁንም ትኩረት ይሻል” - ተመድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:50 0:00

በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይ በጉጂ ዞን የተከሰተው ድርቅ ልዩ ትኩረት እንደሚያስፈለግ ገለፀ።

ቢሮው ዛሬ ባወጣው መግለጫ በተለይ የምግብ እና የመጠጥ ውሃ እጥረት ዋነኛ ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቅሶ አርባ ሁለት በመቶ የሚሆኑ የምዕራብ ጉጂ ነዋሪዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ይፋ አድርጓል።

የጉጅ ዞን ነዋሪዎች በበኩላቸው እየቀረበ ያለው የሰብአዊ ድጋፍ በቂ ያለ መሆኑን ይናገራሉ።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በቀን ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ሕጻናት እንዲያገኙ ለማድረግ መንግስታት በመከተል ላይ ያሉት ልጆችን በትምህርት ቤት የመመገብ ፕሮግራም እጅግ አስፈላጊና በወጪም ረገድ ውጤታማ እንደሆነ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በዓለም ግማሽ የሚሆኑት ተማሪ ልጆች በትምህርት ቤታቸው ምግብ በማግኘት ላይ እንደሆኑና፣ ለምግብ እጥረት እጅግ ተጋላጭ የሆኑ ሊሎች በርካታ ልጆች ግን ለዛ እንዳልታደሉ የምግብ ፕሮግራሙ በመግለጫው አመልክቷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዛሬ ባወጣውና በትምህትርት ቤቶች ህጻናትን መመገብን በተመለከተ ይፋ የሆነው ሪፖርት እንዳመልከከተው በዓለም አቀፍ ደረጃ 420 ሚሊዮን ህጻናት በትምህርት ቤታቸው ምግብ ያገኛሉ።

153 ሚሊዮን ሕጻናትን ጨምሮ 345 ሚሊዮን ሰዎች ረሃብ በተጋረጠባቸው በዚህ ወቅት የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሙ ከፍተኛ ችግር ያለባቸውን ሕጻናት ታድጓል ብሏል ሪፖርቱ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮራም 50 ቢልዮን ዶላር እንደሚፈጀ ያመለከተው ሪፖርት በእአአ 2030 ሁሉንም የትምህርት ቤት ሕጻናት ለመመገብ በተያዘው ዕቅድ ውስጥ 75 መንግስታት ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል ብሏል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG